ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 17:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺህ ተዋጊዎች ጋር፤

17. ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺ ሰዎች ጋር፤

18. ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ጋር፤

19. እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 17