ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 14:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ደካሞችን ከኀይለኞች የሚታደግ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ታምነናልና፣ ይህን ታላቅ ሰራዊት በስምህ እንገጥመዋለን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም።”

12. እግዚአብሔርም ኢትዮጵያውያንን በአሳና በይሁዳ ፊት መታቸው፤ ኢትዮጵያውያኑም ሸሹ፤

13. አሳና ሰራዊቱም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዷቸው፤ እጅግ ብዙ ቊጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ስለወደቁም፣ ሊያንሰራሩ አልቻሉም፤ በሰራዊቱም ፊት ተደመሰሱ። የይሁዳም ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

14. በጌራራ ዙሪያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለወደቀባቸው ከተሞቹን ሁሉ አጠፏቸው፤ እጅግ ብዙ ምርኮም በዚያ ስለ ነበር፣ በዘበዟቸው።

15. እንዲሁም በእረኞች ሰፈር ላይ አደጋ ጥለው እጅግ ብዙ በጎች፣ ፍየሎችና ግመሎች ማረኩ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 14