ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 11:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነዚህንም ምሽጎቻቸውን አጠንክሮ፣ አዛዦችን ሾመባቸው፤ ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸባቸው።

12. በየከተሞቹም ሁሉ ጋሻና ጦር አከማችቶ ይበልጥ አጠና ከራቸው። በዚህ ዐይነት ይሁዳንና ቢንያምን የራሱ አደረገ።

13. በመላው እስራኤል ያሉት ካህናትና ሌዋውያን ከየክልላቸው ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

14. ኢዮርብዓምና ልጆቹ ሌዋውያኑን ከእግዚአብሔር የክህነት አገልግሎት ስላባረሯቸው ሌዋውያኑ ማሰማሪያ ቦታቸውንና ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤

15. እርሱም ለየኰረብታው መስገጃ እንዲሁም ለሠራቸው የፍየልና የጥጃ ምስሎች የራሱን ካህናት ሾመ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 11