ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 9:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም። ከዚያም፣ “ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ናትና ይህችን የተረገመች ሴት በሚገባ ቅበሯት” አለ።

35. ሊቀብሯት ሲወጡ ግን ከራስ ቅሏ፣ ከእግሯና ከእጇ በቀር ሌላ ያገኙት አልነበረም።

36. ተመልሰውም ይህን ሲነግሩት፣ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለባሪያው ለቴስቢያዊው ለኤልያስ፣ ‘በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበሉታል፤

37. ሥጋዋም በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ እንደ ፍግ ስለሚሆን፣ ማንም ሰው፣ ‘ይህች ኤልዛቤል ናት’ ሊል አይችልም ብሎ የተናገረው ቃል ይህ ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 9