ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 3:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፤ የአክአብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ።

2. እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ ክፉ ድርጊቱ ግን አባትና እናቱ እንደ ፈጸሙት ዐይነት አልነበረም፤ አባቱ ያሠራውንም የበኣልን ሐውልት አስወገደ።

3. ነገር ግን የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ባሳተበት ኀጢአት ተያዘ፤ ከዚያም አልተላቀቀም።

4. በዚህ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ ሞሳ በግ ያረባ ነበር፤ እርሱም መቶ ሺህ ጠቦትና የመቶ ሺህ አውራ በግ ጠጒር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር።

5. አክዓብ ከሞተ በኋላ ግን የሞዓብ ንጉሥ በእስራኤል ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

6. ስለዚህ በዚያኑ ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ከሰማርያ ተነሥቶ በመሄድ እስራኤልን ሁሉ አሰባሰበ።

7. ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “የሞዓብ ንጉሥ ስለ ዐመፀብኝ አብረኸኝ ትዘምታለህን?” ሲል መልእክት ላከበት።እርሱም፣ “አዎን አብሬህ እዘምታለሁ፤ እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤ እንደ ሕዝብህ፤ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” በማለት መለሰለት።

8. ኢዮሣፍጥም፣ “የምንዘምተው በየትኛው መንገድ ነው” ብሎ ጠየቀው፤ኢዮራምም “በኤዶም ምድረ በዳ አልፈን ነው” ሲል መለሰለት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 3