ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 18:33-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ለመሆኑ ከአሕዛብ አማልክት ምድሩን ከአሦር ንጉሥ እጅ የታደገ ማን አለ?

34. የሐማትና የአርፋድ አማልክት እስቲ የት አሉ? የሴፈርዋይም፣ የሄናና የዒዋም አማልክት ታዲያ የት ደረሱ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?

35. ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእኔ ለማዳን የቻለ ማን አለ? ታዲያ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊታደጋት እንዴት ይችላል?”

36. ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም፤ ንጉሡ፣ “መልስ እንዳትሰጡ” ሲል አዝዞ ነበርና።

37. ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ፤ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ እንዲሁም ታሪክ ጸሓፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ሕዝቅያስም መጥተው የጦር አዛዡ ያላቸውን ነገሩት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 18