ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 12:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አርባ ዓመት ገዛ። እናቱ ሳብያ የተባለች፤ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች።

2. ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ።

3. ይሁን እንጂ የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በእነዚህ ቦታዎች መሠዋቱንና ማጠኑን እንደ ቀጠለ ነበር።

4. ኢዮአስ ካህናቱን እንዲህ አላቸው፤ “ከሕዝብ ቈጠራ የተገኘውንና በስእለት የገባውን እንዲሁም በራስ ፈቃድ ለቤተ መቅደሱ የተሰጠውን የተቀደሰ ገንዘብ በሙሉ ሰብስቡ።

5. እያንዳንዱም ካህን ገንዘቡን ከገንዘብ ያዡ እጅ ይቀበል፤ እንደ አስፈላጊነቱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል።”

6. ይሁን እንጂ እስከ ሃያ ሦስተኛው የኢዮአስ ዘመነ መንግሥት ካህናቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን አላደሱም ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 12