ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 23:22-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀግንነት እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣

23. ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።

24. ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙ ባቸዋል፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

25. አሮዳዊው ሣማ፣አሮዳዊው ኤሊቃ፣

26. ፈሊጣዊው ሴሌስ፣የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣

27. ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤ኩሳታዊው ምቡናይ፣

28. አሆሃዊው ጸልሞን፣ነጦፋዊው ማህራይ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 23