ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 23:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤“በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

2. “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።

3. የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣

4. እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣እንዳለው ብርሃን ነው፤በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’

5. “የእኔስ ቤት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል አይደለምን?ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን?ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?

6. ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፣በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

7. እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።

8. የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 23