ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 23:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤“በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

2. “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።

3. የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 23