ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤እርሱ ተቈጥቶአልና ራዱ።

9. ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ከውስጡም ፍሙ ጋለ።

10. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

11. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

12. ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።

13. በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።

14. እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።

15. ፍላጻውን ሰድዶ ጠላቶቹን በተናቸው፤መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።

16. ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫውከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣የባሕር ሸለቆዎች ታዩ፤ የምድርመሠረቶችም ተገለጡ።

17. “ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።

18. ከብርቱ ጠላቶቼ፣ከማልቋቋማቸውም ባለጋሮቼ ታደገኝ።

19. በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፈኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22