ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:3-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አምላኬ፣ የምጠጋበት ዐለቴ፣ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው።እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ከኀይለኞች ሰዎች ታድነኛለህ።

4. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርንእጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።

5. “የሞት ማዕበል ከበበኝ፤የጥፋትም ጐርፍ አሰጠመኝ።

6. የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ።

7. በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ወደ አምላኬም ጮኽሁ።እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።

8. “ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤እርሱ ተቈጥቶአልና ራዱ።

9. ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ከውስጡም ፍሙ ጋለ።

10. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

11. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

12. ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።

13. በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22