ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:13-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።

14. እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።

15. ፍላጻውን ሰድዶ ጠላቶቹን በተናቸው፤መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።

16. ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫውከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣የባሕር ሸለቆዎች ታዩ፤ የምድርመሠረቶችም ተገለጡ።

17. “ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።

18. ከብርቱ ጠላቶቼ፣ከማልቋቋማቸውም ባለጋሮቼ ታደገኝ።

19. በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፈኝ።

20. ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።

21. “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤እንደ እጄም ንጹሕነት ብድራትን ከፈለኝ፤

22. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ከአምላኬም ዘወር ብዬ ክፉ ነገር አላደረግሁም።

23. ሕጉ ሁሉ በፊቴ ነው፤ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።

24. በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።

25. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ።

26. “ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ መሆንህን፣ለቅን ሰው አንተም ቅን መሆንህን ታሳያለህ።

27. ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።

28. አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22