ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 9:28-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር፤

29. ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳት፣ ዱቄቱን፣ የወይን ጠጁን፣ የወይራ ዘይቱን፣ ዕጣኑን፣ የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።

30. ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱና ያዘጋጁ ነበር።

31. የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር።

32. በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።

33. የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።

34. እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

35. የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።

36. የበኵር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣

37. ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩር፣ ሚቅሎት ነበሩ።

38. ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

39. ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።

40. የዮናታን ወንድ ልጅ፤መሪበኣል ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።

41. የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

42. አካዝ የዕራን ወለደ፤ የዕራም ናሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።

43. ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁ ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፣ ልጁ ኤሴል።

44. ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 9