ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 9:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።

2. በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጉልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።

3. በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣ የብንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

4. ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ ዘሮች፣ የባኒ ልጅ፣ የአምሪ ልጅ፣ የዖምሪ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።

5. ከሴሎናውያን፦የበኵር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።

6. ከዛራውያን፦ይዑኤል፤የሕዝቡ ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበረ።ከይሁዳ ነገድ የሰው ቊጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበር።

7. ከብንያማውያን፦የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።

8. የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ፣ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የይብንያ ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፣ የሰፋጥያ ልጅ ሜሱላም።

9. በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።

10. ከካህናቱ፦ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤

11. የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።

12. የመልክያ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 9