ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 8:15-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣

16. ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

17. ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣

18. ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።

19. ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣

20. ኤሊዔናይ፣ ጺልታይ፣ ኤሊኤል፣

21. ዓዳያ፣ ብራያና፣ ሺምራት የሰሜኢ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

22. ይሽጳን፣ ዔቤር፣ ኤሊኤል፣

23. ዓብዶን፣ ዝክሪ፣ ሐናን፣

24. ሐናንያ፣ ኤላም፣ ዓንቶትያ

25. ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

26. ሽምሽራይ፣ ሽሃሪያ፣ ጎቶልያ፣

27. ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።

28. እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

29. የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፤ ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።

30. የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣

31. ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና

32. የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

33. ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 8