ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 8:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣

2. አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።

3. የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣

4. አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣

5. ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።

6. በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤

7. ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።

8. ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 8