ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 7:30-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።

31. የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ሐቤርና የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።

32. ሔቤርም ያፍሌጥን፣ ሳሜርን፣ ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።

33. የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ፋሴክ፣ ቢምሃል፣ ዓሲት፤የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ።

34. የሳሜር ወንዶች ልጆች፤አኪ፣ ሮኦጋ፣ ይሑባ፣ አራም።

35. የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ጾፋ፣ ይምና፣ ሰሌስ፣ ዓማል።

36. የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ሱዋ፣ ሐርኔፍር፣ ሦጋል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣

37. ቤጴር፣ ሆድ፣ ሳማ፣ ሰሊሳ፣ ይትራን፣ ብኤራ።

38. የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ዮሮኒ፣ ፊስጳ፣ አራ።

39. የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ።

40. እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺህ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 7