ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 7:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የምናሴ ዘሮች፤ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤

15. ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።

16. የሚኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።

17. የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፤እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤

18. እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና መሕላን ወለደች።

19. የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም።

20. የኤፍሬም ዘሮች፤ሹቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣

21. ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።

22. አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።

23. ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።

24. ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።

25. ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 7