ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 6:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤

9. ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤

10. ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤

11. ዓዛርያስ አማርያን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤

12. አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤

13. ሰሎም ኬልቅያስን ወለደ፤ኬልቅያስ ዓዛርያስን ወለደ፤

14. ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ።

15. እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።

16. የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።

17. የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቤኒ፣ ሰሜኢ።

18. የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 6