ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 6:64-74 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

64. እስራኤላውያንም ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።

65. ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው መደቡላቸው።

66. ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ቦታ ተሰጣቸው።

67. በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣

68. ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣

69. ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

70. እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።

71. ጌድሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

72. ከይሳኮርም ነገድ፣ቃዴስን፣ ዳብራትን

73. ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

74. ከአሴር ነገድመዓሳልን፣ ዓብዶን፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 6