ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 6:3-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የእምበረም ልጆች፤አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም።የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣ አብዮድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።

4. አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤

5. አቢሱ ቡቂን ወለደ፤ቡቂ ኦዚን ወለደ፤

6. ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤

7. መራዮት አማርያን ወለደ፤አማርያ አኪጦብን ወለደ፤

8. አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤

9. ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤

10. ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤

11. ዓዛርያስ አማርያን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤

12. አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤

13. ሰሎም ኬልቅያስን ወለደ፤ኬልቅያስ ዓዛርያስን ወለደ፤

14. ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 6