ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 6:27-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።

28. የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።

29. የሜራሪ ዘሮች፤ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣

30. ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።

31. ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤

32. እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።

33. ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣

34. የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ

35. የሱፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣የመሐት ልጅ፣ የአማሢ ልጅ፣

36. የሕልቃና ልጅ፣ የኢዮኤል ልጅ፣የዓዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣

37. የታሐት ልጅ፣ የአሴር ልጅ፣የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣

38. የይስዓር ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ።

39. እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣

40. የሚካኤል ልጅ፣ የበዓሤያ ልጅ፣የመልክያ ልጅ፣

41. የኤትኒ ልጅ፣የዛራ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣

42. የኤታን ልጅ፣ የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣

43. የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፤

44. በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣

45. የሐሸብያ ልጅ፣የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣

46. የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣የሴሜር ልጅ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 6