ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 6:24-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ልጁ ኢኢት፣ ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል።

25. የሕልቃና ዘሮች፤አማሢ፣ አኪሞት።

26. ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣

27. ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።

28. የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።

29. የሜራሪ ዘሮች፤ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣

30. ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።

31. ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤

32. እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 6