ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 5:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለ ነበር በምሥራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።

10. በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።

11. የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤

12. አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚያም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ።

13. ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተ ሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፤ ባጠቃላይ ሰባት ነበሩ።

14. እነዚህ ደግሞ የቡዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጅ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 5