ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 3:8-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9. ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።

10. የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤የሮብዓም ልጅ አቢያ፣የአቢያ ልጅ አሳ፣የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

11. የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣

12. የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣

13. የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣

14. የምናሴ ልጅ አሞጽ፣የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ።

15. የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤በኵሩ ዮሐናን፣ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣አራተኛ ልጁ ሰሎም።

16. የኢዮአቄም ዘሮች፤ልጁ ኢኮንያ፣ልጁ ሴዴቅያስ።

17. የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ልጁ ሰላትያል፣

18. መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።

19. የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ።የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤ሜሱላም፣ ሐናንያ፤እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።

20. ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።

21. የሐናንያ ዘሮች፤ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።

22. የሴኬንያ ዘሮች፤ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ ባጠቃላይ ስድስት ነበሩ።

23. የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ ባጠቃላይ ሦስት ነበሩ።

24. የኤልዩዔናይም ወንዶች ልጆች፤ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ ባጠቃላይ ሰባት ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 3