ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 3:3-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ፣ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።

4. እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤

5. በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።

6. እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣

7. ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣

8. ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9. ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።

10. የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤የሮብዓም ልጅ አቢያ፣የአቢያ ልጅ አሳ፣የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

11. የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣

12. የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣

13. የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣

14. የምናሴ ልጅ አሞጽ፣የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ።

15. የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤በኵሩ ዮሐናን፣ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣አራተኛ ልጁ ሰሎም።

16. የኢዮአቄም ዘሮች፤ልጁ ኢኮንያ፣ልጁ ሴዴቅያስ።

17. የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ልጁ ሰላትያል፣

18. መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 3