ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 3:2-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣

3. አምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ፣ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።

4. እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤

5. በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።

6. እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣

7. ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣

8. ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9. ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።

10. የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤የሮብዓም ልጅ አቢያ፣የአቢያ ልጅ አሳ፣የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

11. የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣

12. የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 3