ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 3:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የበኵር ልጁ አምኖን፣ሁለተኛው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣

2. ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣

3. አምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ፣ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።

4. እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤

5. በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።

6. እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣

7. ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣

8. ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9. ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።

10. የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤የሮብዓም ልጅ አቢያ፣የአቢያ ልጅ አሳ፣የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 3