ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 27:22-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።

23. እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር።

24. የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቊጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቊጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።

25. የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።

26. የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።

27. ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

28. ጌድራዊው በአልሐናን በምራባዊው ኰረብታዎች ግርጌ ለሚግኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ።

29. ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።

30. እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ።ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።

31. አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።

32. አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።

33. አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።

34. የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ።ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 27