ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 27:17-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።

18. በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።

19. በዛብሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።

20. በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ፤በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።

21. በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል።

22. በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።

23. እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር።

24. የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቊጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቊጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።

25. የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።

26. የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።

27. ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

28. ጌድራዊው በአልሐናን በምራባዊው ኰረብታዎች ግርጌ ለሚግኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ።

29. ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 27