ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 24:18-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ወጣ።

19. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።

20. ከቀሩት የሌዊ ዘሮች ደግሞ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።

21. ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤አለቃው ይሺያ።

22. ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚትከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።

23. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።

24. የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ።ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።

25. የሚካ ወንድም ይሺያ፤ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።

26. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ።

27. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።

28. ከሞሖሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።

29. ከቂስ፤ የቂስ ወንድ ልጅ፤ይረሕምኤል።

30. የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት።እነዚህ እንግዲህ እንደየቤተ ሰባቸው የተቈጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።

31. ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 24