ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 23:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የእንበረም ወንዶች ልጆች፤አሮን፣ ሙሴ።አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።

14. የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15. የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ጌርሳም፣ አልዓዛር።

16. የጌርሳም ዘሮች፤ሱባኤል።

17. የአልዓዛር ዘሮች፤የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።

18. የይስዓር ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሰሎሚት።

19. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።

20. የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 23