እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር አምላካችሁ እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ሰጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ተገዝታለች።