ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 22:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀህ ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርታ፤ ተስፋም አትቊረጥ።

14. “ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺህ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ። በተረፈ አንተ ጨምርበት።

15. ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣ አናጢዎች የሆኑ ብዙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 22