ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 17:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።

2. ናታንም ለዳዊት፣ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ፣ ያሰብከውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።

3. በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤

4. “ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።

5. እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱ ማደሪያ ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣ በቤት ውስጥ አልኖርሁም።

6. ከእስራኤላውያን ጋር በሄድሁባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሪዎቻቸው ከቶ፣ “ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሠራችሁልኝም ያልሁበት ጊዜ አለን?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 17