ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 13:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ።

2. ከዚያም ለመላው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፣ በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞችና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክባቸው።

3. በሳኦል ዘመነ መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ”።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 13