ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 11:25-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ክሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።

26. ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

27. ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌድ፣

28. የቴቊሔ ሰው የሆነው የዒስካ ልጅ፣ዒራስ፣ የዓናቶቱ ሰው አቢዔዜር፣

29. ኩሳታዊው ሴቤካይ፣አሆሃዊው ዔላይ፣

30. ነጦፋዊው ማህራይ፣የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣

31. ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታይ፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣

32. የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣

33. ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣

34. የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣

35. የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣

36. ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣

37. ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤

38. የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣

39. አሞናዊው ጼሌቅ፣የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ነሃራይ፣

40. ይትራዊው ዒራስ፣ይትራዊው ጋሬብ፣

41. ኬጢያዊው ኦርዮ፣የአሕላይ ልጅ ዛባድ፣

42. የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፤እርሱም የሮቤላውያንና አብረውትለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 11