ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 11:17-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣ “ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

18. በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጒድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤

19. ከዚያም “ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ፤ ይህ በሕይወታቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?” አለ። ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቈርጠው ስለ ነበር፣ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።ሦስቱ ኀያላን ሰዎች የሠሩት ይህንን ነበር።

20. የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።

21. ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ እጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።

22. ከቀብስኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጒድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።

23. ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊ ገደለ፤ ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቆመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።

24. የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ።

25. ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ክሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።

26. ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

27. ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌድ፣

28. የቴቊሔ ሰው የሆነው የዒስካ ልጅ፣ዒራስ፣ የዓናቶቱ ሰው አቢዔዜር፣

29. ኩሳታዊው ሴቤካይ፣አሆሃዊው ዔላይ፣

30. ነጦፋዊው ማህራይ፣የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣

31. ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታይ፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 11