ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 1:6-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የጋሜር ወንዶች ልጆች፤አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቴርጋማ።

7. የያዋን ወንዶች ልጆች፤ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ።

8. የካም ወንዶች ልጆች፤ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን።

9. የኩሽ ወንዶች ልጆች፤ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ።የራዕማ ወንዶች ልጆች፤ሳባ፣ ድዳን።

10. ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያውኀያል ጦረኛ ሆነ።

11. ምጽራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣

12. የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂ ማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።

13. ከነዓን የበኵር ልጁ የሆነው የሲዶን እንዲሁም የኬጢያውያን፣

14. የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣

15. የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣

16. የአራዴዎያውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።

17. የሴም ወንዶች ልጆች፤ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም።የአራም ወንዶች ልጆች፤ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።

18. አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ሳላም ዔቦርን ወለደ።

19. ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

20. ዮቅጣንም፡አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣

21. ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 1