ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 1:38-49 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. የሴይር ወንዶች ልጆች፤ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።

39. የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ሖሪ፣ ሄማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

40. የሦባል ወንዶች ልጆች፤ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ፣ አውናም።የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤አያ፣ ዓና።

41. የዓና ወንድ ልጅ፤ዲሶን።የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።

42. የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን።የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ዑፅ፣ አራን።

43. በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማዪቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።

44. ባላቅ ሲሞትም የባሶራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

45. ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

46. ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማዪቱም ስም ዓዊት ተባለ።

47. ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

48. ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሚቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

49. ሳኡልም ሲሞት የዓክቦር ልጅ የሆነው በኣልሐናንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 1