ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 6:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የምድር ቤቱ መግቢያ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ ጐን ሲሆን ወደ መካከለኛውና ከዚያም ወደ መጨረሻው ፎቅ የሚያስወጣ ደረጃ ነበረው።

9. ቤተ መቅደሱንም በዚሁ ሁኔታ ሠርቶ ጨረሰ፤ ለጣራው ተሸካሚ አደረገለት፤ በዝግባ ሳንቃም ከደነው።

10. በቤተ መቅደሱም ዙሪያ በሙሉ፣ ቁመታቸው አምስት አምስት ክንድ የሆነ ክፍሎች ሠራ፤ እነዚህንም ከቤተ መቅደሱ ጋር በዝግባ አግዳሚ ዕንጨቶች አያያዛቸው።

11. የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰሎሞን መጣ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 6