ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 5:10-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በዚህ ሁኔታ ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የዝግባና የጥድ ግንድ በሙሉ ያቀርብለት ጀመር፤

11. ሰሎሞን ደግሞ ለኪራም ቤተ ሰው ቀለብ እንዲሆን ሃያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ ሃያ ሺህ ኮር ንጹሕ የወይራ ዘይት ሰጠው፤ ይህን ባለማቋረጥ በያመቱ ለኪራም ይሰጥ ነበር።

12. እግዚአብሔርም በገባለት ተስፋ መሠረት ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከልም መልካም ግንኙነት ነበር፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

13. ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል የጒልበት ሠራተኞችን መለመለ፤ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ነበር።

14. እነዚህንም አንድ ወር በሊባኖስ እንዲሠሩ፣ ሁለት ወር በቤታቸው እንዲያርፉ በማድረግ፣ ዐሥር ዐሥር ሺዉን ወር ተራ አግብቶ ላካቸው። የጒልበት ሠራተኞቹም አለቃ አዶኒራም ነበር።

15. ሰሎሞንም በኰረብታማው አገር ሰባ ሺህ ተሸካሚዎችና ሰማንያ ሺህ ድንጋይ ጠራቢዎች ነበሩት፤

16. እንዲሁም ሥራውን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ኀላፊዎች ነበሩ።

17. እነርሱም በንጉሡ ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆን ታላላቅና ምርጥ ድንጋይ ፈልፍለው በማውጣት የተጠረበ ድንጋይ አዘጋጁ።

18. የሰሎሞንና የኪራም የእጅ ባለ ሙያዎች እንዲሁም የጌባል ሰዎች ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ዕንጨትና ድንጋይ ፈልጠው አዘጋጁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 5