ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 22:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በሶርያና በእስራኤል መካከል ለሦስት ዓመት ጦርነት አልነበረም።

2. በሦስተኛው ዓመት ግን የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ ለመጐብኘት ወረደ።

3. የእስራኤልም ንጉሥ ሹማምቱን፣ “በገለዓድ የምትገኘው ሬማት የእኛ ሆና ሳለች፣ ከሶርያው ንጉሥ እጅ ለመመለስ ምንም እንዳላደረግን አታውቁምን?” አላቸው።

4. ስለዚህ ኢዮሣፍጥን፣ “በገለዓድ የምትገኘው ሬማት ላይ ለመዝመት አብረኸኝ ለመሄድ ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀው።ኢዮሣፍጥም፣ “እኔ ያው እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤ እንደ ሕዝብህ፣ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 22