ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 18:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ታዲያ አንተ ሄጄ ለጌታዬ፤ ‘ኤልያስ እዚህ አለልህ’ እንድለው ትፈልጋለህ፤ እርሱም ይገድለኛል!”

15. ኤልያስም፣ “በፊቱ የቆምሁት ሁሉን የሚገዛ ጌታ እግዚአብሔርን፣ ዛሬ በአክዓብ ፊት በርግጥ እገለጣለሁ” አለ።

16. ስለዚህ አብድዩ ሄዶ ይህንኑ ለአክዓብ ነገረው፤ አክዓብም ኤልያስን ለማግኘት ሄደ።

17. ኤልያስንም ባየው ጊዜ፤ “እስራኤልን የምታውክ አንተ ነህን?” አለው።

18. ኤልያስም መልሶ እንዲህ አለ፤ “አንተና የአባትህ ቤት እንጂ እኔ እስራኤልን አላወክሁም። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተዋችሁ፣ እነ በኣልንም ተከተላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 18