በዛሬው ቀን ታች ወርዶ ብዙ በሬዎች፣ ኮርማዎችና በጎች ሠውቶአል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሰራዊቱን አዛዦችና ካህኑን አብያታርንም ጠርቶአል፤ እነሆ፤ አሁን፣ ‘አዶንያስ ለዘላለም ይኑር’ እያሉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።