የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱ ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ወደ ቦታው መለሱት።