ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 3:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ዔሊም፣ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድ ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው።

18. ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ።

19. ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፣ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።

20. ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል በርግጥ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።

21. እግዚአብሔር በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 3