ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 20:21-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ከዚያም፣ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፣ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ አደጋም የለም፤ ውጣና ና።

22. ነገር ግን ልጁን፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደሆነ እግዚአብሔር እንድትሄድ ፈቅዶአልና ሂድ።

23. አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ እግዚአብሔር በመካከላችን ለዘላለም ምስክር ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 20