ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺህ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፣ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።